በአሜሪካ ስብሰባ ላይ የሚገኙት አቶ መለስ ዜናዊ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ገና መናገር ሲጀመሩ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከፍ ባለ ድምፅ፤ “ይህ ሰው ነብሰ ገዳይ ነው… ወንጀለኛ ነው… እዚህ ቦታ ሊገኝ አይገባውም” ሲል በተሰብሳቢዎች ፊት ተቃውሞውን አሰማ ሲል ኢሳት ዘገበ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዳራሽ ውስጥ እንዲህ ያለ የተቃውሞ ያጋጥመኛል ብለው ስላላጠበቁ ተደናግጠው ንግግራቸውን አቆርጠው እንደነበር ኢሳት በዘገባው ገልጿል።አበበን የፀጥታ ሀይሎች በሰላም ከአዳርሽ እንዲወጣ እንዳደረጉት ኢሳት ገልጿል።
አቶ መለስ በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ንግግር
ለማድረግ ሲሄዱ ተቃውሞ ሲገጥማቸው የመጀመርያው ባይሆንም የጋዜጠኛ አበበ ገላው ጠቃውሞ ግን አቶ መለስን ያስደነገጠ እና በአቶ
መለስ ላይ ተቃውሞው መጠንከሩን ለአለም ህብረተሰብ ያሳየ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ።
No comments:
Post a Comment