Friday, May 18, 2012

ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከፍ ባለ ድምፅ ያሰማውን ተቃውሞ በቪዲዮ ይመልከቱ ::Ethiopian Journalist Abebe Gellaw Confronted Meles Zenawi (Video)


BREAKING NEWS በአሜሪካ ስብሰባ ላይ የሚገኙት አቶ መለስ ዜናዊ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ገና መናገር ሲጀመሩ በጋዜጠኛ አበበ ገላው ከፍ ባለ ድምፅ ተቃውሞ ገጠማቸው



በአሜሪካ ስብሰባ ላይ የሚገኙት አቶ መለስ ዜናዊ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ገና መናገር ሲጀመሩ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከፍ ባለ ድምፅ፤  “ይህ ሰው ነብሰ ገዳይ ነውወንጀለኛ ነውእዚህ ቦታ ሊገኝ አይገባውምሲል በተሰብሳቢዎች ፊት ተቃውሞውን አሰማ ሲል ኢሳት ዘገበ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዳራሽ ውስጥ እንዲህ ያለ የተቃውሞ  ያጋጥመኛል ብለው ስላላጠበቁ ተደናግጠው ንግግራቸውን አቆርጠው እንደነበር  ኢሳት በዘገባው ገልጿል።አበበን የፀጥታ ሀይሎች በሰላም ከአዳርሽ እንዲወጣ እንዳደረጉት ኢሳት ገልጿል።
አቶ መለስ በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ንግግር ለማድረግ ሲሄዱ ተቃውሞ ሲገጥማቸው የመጀመርያው ባይሆንም የጋዜጠኛ አበበ ገላው ጠቃውሞ ግን አቶ መለስን ያስደነገጠ እና በአቶ መለስ ላይ ተቃውሞው መጠንከሩን ለአለም ህብረተሰብ ያሳየ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ።