Saturday, April 14, 2012

የአወልያው ተቃውሞ ወደ አንዋር መስኪድ ተዘዋወረ።


 በአወሊያ ትምህርት ቤት ከሁለት ወራት ላላነሰ ጊዜ ተቃውሞዋቸውን ሲያሰሙ የነበሩት የሙስሊሙ ማሕበረሰብ አባላት አርብ ሚያዚያ 5 ቀን በታላቁ አንዋር መስኪድ መንግስትን እና ከመንግስት ጋር ቅርበት ያላቸው የመጅሊስ አመራሮች ላይ ተቃውሞ አደረጉ።  “አህባሸን አስተምህሮት ለማስፋፋት ጥረት እያደረጉ ነው” ባሏቸው የመጅሊስ አመራሮች ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል።

ከአዲስ አበባ ተገኙ መረጃዎ እንደሚስረዱት በአወሊያ ተጀመረው ተቃውሞ በመጠናከር በአንዋር መስኪድ መቀጠሉን የተመለከተው መንግስት ተቃውሞው እንዳይስፋፋ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማግባባት ብሎም ለማስፈራራት ቢሞክርም ተቃውሞው ከጊዜ ወደ ጊዜ እጠነከረ መምቱን እነዚሁ መረጃዎች ስረዳሉ።

ከሙስሊሞቹ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ተቃውሞውን ያስተባብራሉ ባላቸው ግለሰቦች ላይ መንግስት ከፍተኛ ክትትል እደረገ መሆኑን ውስጥ ምንጮች ገልፃሉ። በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በመጅሊስ አመራሮች መሃል ያለው አለመግባባት ያሰጋው መንግስት ሙስሊሞቹን ጥያቄ በተለየ መንገድ ለማፈን ሲሞክር ተስተውሏል። “ለጋዜጠኞች እና ለፖለቲከኞች ሲጠቀምበት ነበረውን ሽብርተኝነት ወደ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ አዙሯል” ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ። ሰሞኑን በሽብርተኝነት የተከሰሱት የሙስሊም ማሕበረሰብ አባላት የዚህ ጉልህ ማሳያ እንደሆኑ እነዚሁ ወገኖች ይገልጻሉ።

No comments: