Saturday, May 5, 2012

በአቶ መለስ መንግስትና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል



ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ /  
የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ ኮሚቴ፤በሀሰት ፕሮፓገጋንዳ የመብት ጥያቄዎቻችን አይዳፈኑም”  በሚል ርዕስ ባለ 15 ገጽ መግለጫ በበተነበት በትናንትናው ዕለት፤ መንግስት  በተቃራኒው የማስጠንቀቂያ እና የማስፈራሪያ መግለጫ አወጣ ሲል ኢሳት ዘገበ።
 የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርን ዋቢ ያደረገው ይህው የኢሳት ዘገ ባ መንግስት ያወጣውን መግለጫ፤ በሙስሊም  ህብረተሰብ  ዘንድ እየተነሳ ያለውን ጥያቄና ተቃውሞ፤ በምርጫ 97 ወቅት ተከስቶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር አመሳስሎታል ብሏል።
 “መንግስት  ለእስልምና እምነትና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ካለው አክብሮት በመነሳት  እያሳዬ ያለው ሰፊ ትዕግስት፤ የተቃውሞው አስተባባሪ የሆነው  ህገ ወጥ ሀይል  ከፍርሀት እየተመለከተው  ነውሲልም- የአቶ መለስ መንግስት አለመፍራቱን ጠቅሷል።
 እንደ መንግስት መግለጫ፤ ላለፉት 11 ሳምንታት አወሊያ እና በአንዋር መስጊድ  እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ   የብዙሀኑ ሙስሊም ጥያቄ ሳይሆን፤ህግና ስርዓትን አክብረው ለመሄድ ዝግጁነት በሌላቸው ሀይሎች  የሚመራ ነው።
 “ እነዚህ ወገኖች  መንግስትም ሆነ የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም የየራሳቸውን ምላሽ እንዳልሰጧቸው በማስመሰል ሰፊ አፍራሽ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እያካሄዱ ከመሆኑም በላይ፤ 1997 ሀገሪቱን ለብጥበጥ ዳርገው ከፍ ያለ ጉዳት ካደረሱትና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተመደቡ ሀይሎች የጥፋት እንቅስቃሴ ጋር በግላጭ ተመጋጋቢ የሆነ ዘመቻም እያካሄዱ ነውሲልምየሀይማኖታችን ይከበር!’ ጥያቄ ባነሱ ሙስሊሞች ላይ ፖለቲካዊ ክስ አሰምቷል።
መግለጫው አያይዞም፦መንግስት ያሳየውን ትእግስት ከድክመት በመቁጠር መንግስት ፀረ ህገ መንግሰት ሆኗል-ስለዚህ በህገ መንግስቱ የተጎናፀፍናቸውን መብቶች ሊነጥቀን ተነስቷል በማለት እየተቀሰቀሰ ነውብሏል።
 እነዚህ ወገኖች ፖል ቶክና ፌስቡክን የመሳሰሉ ዘመናዊ ሚዲያዎችን ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ በማዋል ግርግርና ሁከት እንዲስፋፋ ከሚሹ በሀገር ውስጥ በሚነገሩ ቋንቋዎች ከሚተላለፉ የውጭ ሚዲያዎች ጋር በመቀናጀት በሀገሪቱ መንግስት ላይ የሚያካሂዱት የማጥላላት ዘመቻ መረን የለለቀበበት ደረጃ ደርሷል ሲልም- የፌዴራል ጉዳዮች መግለጫ አብራርቷል።
 በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ የተደነገገ ቢሆንም፤ አቶ መለስና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአህባሽን አስተምህሮ እንዲከተሉ፤ እንዲሁም ባልመረጧቸውና አይወክሉንም ባሏቸው የመጂሊስ አመራሮች እንዲመሩ ግፊት በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።
 የተቃውሞው መንስኤም ሆነ እስካሁን ድረስ ህዝበ-ሙስሊሙ በሚያደርጋቸው ተቃውሞዎች እያቀረባቸው ያሉት ጥያቄዎችም በዋነኝነት ከነዚሁ ሁለት ነጥቦች ጋር የተያያዘ ነው- ያልመረጥነው የመጂሊስ አመራር ይነሳልን! መንግስት የአህባሽን አስተምህሮ በግዳጅ ህዝበ-ሙስሊሙ ላይ ለመጫን ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ያቁም!” የሚሉ።
 የህዝበ-ሙስሊሙ ጥያቄዎች  በሀይማኖታዊ መብት መከበር ዙሪያ ላይ ያነጣጠሩ ከመሆናቸውም በላይ እስከዛሬ ድረስ በመስጂዳቸው ተወስነው ባሰሙት ተቃውሞ  በተደጋጋሚ፦መንግስት ድምፃችንን ይስማ!” እያሉ ሲጠይቁ መደመጣቸው ይታወቃል።
 የአቶ መለስ መንግስት ፤አንድ ጊዜ ከአክራሪዎችና ከአሸባሪዎች፤ ሌላ ጊዜ ከተቃዋሚ ሀይሎችናኪራይ ሰብሳቢዎችከሚላቸው ወገኖች ጋር እያገናኘ ፖለቲካዊ ምስል እየሰጠው ያለው ፤ይህንየሀይማኖታዊ መብት ይከበር!” ጥያቄ ነው።
ከዚህም አልፎ በአርሲ-አሰሳ ከተማ በመስጊዳቸው ተወስነው የተቃውሞ ድምጽ ሲያሰሙ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ከፍተው ሰባት መግደላቸው እና በርካቶችን ማቁሰላቸው ይታወሳል።
 ግድያውን ተከትሎ  ትናንት የፌዴራል ጉዳዮች ያወጣው መግለጫ፤መንግስት መጠነ ሰፊ የሀይል እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን የሚያመለክት ነው።
 የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ ኮሚቴ ደግሞ፦በሀሰት ክስና ፕሮፓጋንዳ የሙስሊሙን ጥያቄ አዳፍናለሁ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ  መሆኑን ነው ያሰመረበት።
 “ እውነትን እስከያዝን ድረስ፤በሀሰት ተወንጅለን እንታሰራለን ብለን አንፈራም! እንሞታታለን እንጂ ከመብት ጥያቄያችን ወደ ሁዋላ አናፈገፍግምነው  እያሉ  ያሉት ብዙሀኑ ሙስሊሞች።
 ለዚህም ይመስላል አሰሳ ሰባት ሙስሊሞች  በተገደሉና ሳምንት እና መንግስት  የማስጠንቀቂያ መግለጫ ባወጣ ማግስት  በዋለው በዛሬው የጁምአ ጸሎት እንደ ወትሮው ሁሉ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሙስሊሞች  ጠንካራ የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።
 ለመንግስት መግለጫ ቀጥተኛ ምላሽ በሚመስል መልኩ መቶሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአንዋር መስኪድ ተገኝተው በአርሲ አሳሳ ከተማ የተገደሉት ሰዎች አሸባሪዎች አለመሆናቸውን እና የመጅሊስ አመራሮችም ከስልጣን ወርደው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። ድርጊቱን በስፍራው ተገኝቶ በፊልም የቀረጸው የኢሳት ዘጋቢ እንዳለው በዛሬው እለት የነበረው ተቃውሞ ሙስሊሙ ማህበረሰብ መንግስት ላወጣው መግለጫ ቁብ እንዳልሰጠው የሚያመለክት ነው።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎፋ አካባቢ በሚገኘው ጀሙ መስጊድ ሌሊቱን ከፍተኛ የሆነ ተኩስ እንደነበር፣ በአካባቢው የሚገኙ የሙስሊም መሪዎችን ለመያዝ ጥረት መደረጉን ለማወቅ ተችሎአል። በሼክ ኮጀሌ መስጊድ ደግሞ 10 ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። አዎልያ ኮሌጅም ዛሬ ተዘግቶ መዋሉን መረጃዎች ደርሰውናል። መረጃዎቹን ከመንግስት በኩል ለማጣራት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።  

Thursday, May 3, 2012

“የመለስ አምልኮ” የሚል ርእስ ያለው መጽሀፍ ነገ በገበያ ላይ ይውላል


ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣ መሥራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጋዜጣ ላይ ያወጣቸውን ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ፊቸር- ጽሑፎች፣ አርቲክሎች እና ሀገራዊ ኮሜንተሪ- ሂሶች “የመለስ አምልኮ” በሚል ርዕስ የተመረጡ ስብስብ ሥራዎቹን በመድብል መልክ ያዘጋጀ ሲሆን መጽሐፉ በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ዋና- ዋና ከተሞች በገበያ ላይ ይውላል፡፡
“የመለስ አምልኮ” መጽሐፍ 255 ገፆችን አካቶ በመጸሐፉ ጀርባ ላይ የቀድሞው የኢፌድሪ ፕሬዝዳንትና በአሁኑ ጊዜ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ  ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እና በመካከለኛው ምሥራቅ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ወኪል የሆነው ነቢዩ ሲራክ-ን አወንታዊ አስተያየት አካቶ ይዞ ለሀገር ውስጥ በ39 ብር ዋጋ በስርጭት ላይ ያገኛል ያሉን ለአሳታሚው ቅርበት ያላቸው ምንጮች በቁጥር ከ15 ሺህ እስከ 20 ሺህ አካባቢ ለመጀመሪያ ሕትመት የበቃ እና በሀገራችን በጋዜጣ ፍጆታ የዋሉ ፊቸር- አርቲክሎች ይታተሙበት ከነበረው ቁጥር የላቀ ነው ብለዋል፡፡
መጽሐፉ በክፍል አንድ “ሀገራዊ ጉዳዮች” በሚለው ውስን ርዕስ ውስጥ ስድስት ፊቸር-አርቲክሎችን የያዘ ሲሆን፡-  “ይድረስ ለአጉራ ዘለል ካድሬ፣ ኢትዮጵያዊው ማነው፣ የሀገር ፍቅር እስከምን ድረስ፣ “ፌዴራሊዝም” ይሄ ከሆነማ፣ ኪራይ ሰብሳቢ ስንል፣ የትግራይ ህዝብ ማነው” ፣ በክፍል ሁለት “የገዢዎች ጦማርና ባህሪያቶቻቸው” በሚለው ንኡስ ርዕስ ውስጥ ደግሞ- “መለስ ዜናዊ ከመይ ቀኒዮም፣ አቦይ ስብሃት ነጋን በጨረፍታ፣ ምነው አባታችን እያወቁ፣ የሀውልቱ ሥር ፖለቲካ፣ ልጆቻችሁ ቻይና ምን እየሰሩ ነው እና የመጽሐፉ ዋቢ ርዕስ የሆነው የመለስ አምልኮ” ይገኝበታል፡፡
በክፍል ሦስት- “ታላላቅ ሀገራዊ ክስተቶች” ንኡስ  ርዕስ ውስጥ ደግሞ- ትዝታ ሚያዚያ 30፣ የፕሮፌሰር አስራት ወይስ የመኢአድ ሙት ዓመት፣ እስክንድር ነጋን ሳስበው ሳስበው ክፍል አንድ፣ ሰኞን ከመለስ ዜናዊ ጋር፣ ኢህአዴግ ምን ያድርግህ፣ ጓደኞቼን መልሱልኝ፣ አኪልዳማው የአይሁድ ወይስ የኢህአዴግ” የሚሉ ፊቸር- አርቲክሎች ተካተውበታል፡፡
በክፍል አራት- “አንዳንድ ነጥቦች ስለፓርቲዎቻችን” ውስን ርዕስ ውስጥ ደግሞ “ኢህአዴግና ሙስና የአንድ ሳንቲም ግልባጮች፣ የብአዴን ሰዓት ስንት ላይ ቆሟል፣ የተቃዋሚዎች ሰፈር እንደምን ከረመ፣ ኦህዴድን በጨረፍታ፣ ኢህአዴግ አውራ ፓርቲ ሲል” የሚሉ አምስት ፊቸር- አርቲክሎችን ይዟል፡፡
በክፍል አምስት “ሕዝባዊ ብሶቶች” በሚለው የመጨረሻው ንኡስ ርዕስ ውስጥ ደግሞ  “ኢትዮጵያኒዝም” ወደ “ቱኒዚያኒዝም” ያልተቋጨው የአብዮቶች ዋዜማ፣ የፀጥታ ጩኸት፣ “ሹክሹክታው” ምንድን ነው፣ እኔም “አሸባሪ ነኝ”፣ ቄሳርም ይደነግጣል፣ ሞት የማይፈሩ ወጣቶች- የሚሉ ከዚህ ቀደም በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተስተናገዱ ፊቸር- አርቲክሎች ይገኙበታል፡፡

Wednesday, May 2, 2012

Eskinder honored with Pen America's "Freedom to Write" Award


Serkalem Fasil receives the award on behalf of her husband, Eskinder Nega (Pen/AP)
Eskinder smiles as he comforts his crying son, Nafkot. The miracle child was born in prison in 2006 when his mom, award-winning journalist Serkalem Fasil was also behind bars for the same reason as her husband.
NEW YORK 
By Associated Press | May 2, 2012


— An imprisoned Ethiopian journalist and blogger who could face the death penalty for advocating peaceful protests in his Horn of Africa homeland was honored Tuesday with PEN America’s “Freedom to Write” award.

Eskinder Nega was arrested in 2011 under Ethiopia’s sweeping anti-terrorism laws, which PEN says criminalize any reporting deemed to “encourage” or “provide moral support” to groups and causes the government deems “terrorists.”
Nega is still in jail after a judge in Addis Ababa found him guilty Jan. 23 on terror charges. He could face the death penalty at sentencing.
Ethiopia has arrested close to 200 people, among them journalists and opposition politicians and members, under last year’s anti-terrorism proclamation.
According to the Committee to Protect Journalists, more journalists have fled Ethiopia than any other country in the world over the past decade.
Nega was honored at PEN/America’s annual gala dinner Tuesday at the American Museum of Natural History, with some 500 PEN members and supporters in attendance.
PEN/America granted him the year’s PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award.
Forty-six women and men have received the award since 1987; 33 of the 37 honorees who were in prison at the time they were honored were subsequently released.
Accepting the award was his wife, Serkalem Fasil, a free expression advocate in her own right, who served 17 months in prison for treason starting in 2005 and gave birth to their child behind bars. She won the International Women’s Media Foundation Courage in Journalism Award in 2007.
“The Ethiopian writer Eskinder Nega is that bravest and most admirable of writers, one who picked up his pen to write things that he knew would surely put him at grave risk,” said Peter Godwin, president of PEN American Center. “Yet he did so nonetheless. And indeed he fell victim to exactly the measures he was highlighting, Ethiopia’s draconian ‘anti terrorism’ laws that criminalize critical commentary.”
Nega has been publishing articles critical of the government since 1993, when he opened his first newspaper, Ethiopis, which was soon shut down by authorities.
He was the general manager of Serkalem Publishing House, which published the newspapers Asqual, Satenaw, and Menelik, all of which are now banned in Ethiopia.
Nega has also been a columnist for the monthly magazine Change and the U.S.-based news forum EthioMedia, which are also banned in Ethiopia.
He has been detained at least seven times under Prime Minister Meles Zenawi, including in 2005, when he and his wife Serkalem were imprisoned for 17 months on treason charges for their critical reporting on the government’s violent crackdown of protests following disputed elections, and briefly in February 2011 for “attempts to incite Egyptian and Tunisian-like protests in Ethiopia” after he published articles on the Arab uprisings.
Nega has been denied a license to practice journalism since 2005, yet he has continued to publish columns critical of the government’s human rights record and calling for an end to political repression and corruption.
Nega was again arrested Sept. 14, 2011, after he published a column questioning the government’s claim that a number of journalists it had detained were suspected terrorists, and for criticizing the arrest of well-known Ethiopian actor and government critic Debebe Eshetu on terror charges earlier that week.
Shortly after his arrest, Nega was charged with affiliation with the banned political party Ginbot 7, which the Ethiopian government considers a terrorist organization. On Nov. 10, Nega was charged and further accused of plotting with and receiving weapons and explosives from neighboring Eritrea to carry out terrorist attacks in Ethiopia. State television portrayed Nega and other political prisoners as “spies for foreign forces.”
He is being held in Maekelawi Prison in Addis Ababa, where detainees are reportedly often tortured.



Monday, April 30, 2012

ሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል



በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣  ሁለት የውጭ ሀገር ተወላጆች  ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል ሲል ኢሳት ዘገበ።
የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት የውጭ ሀገር ተወላጆች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ ከህዝብ ጋር አንጣላም” በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት  ምእርባዊያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም።
5 ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በዋልድባ ተገኝተው ተቃውሞ እያሰሙ ባለበት በዚህ ጊዜ፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትም እርምጃ ለመውሰድ ፈርተዋል።ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ነው፣ መንግስትና ህዝቡ ተፋጠዋል፣ የአካባቢው ወጣቶችም ወደ አካባቢው ለመጓዝ እየተመካከሩ ነው” ሲል አንድ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተል ሰው  ገልጧል ሲል ኢሳት በዘገባው ገልጿል።
 ለህዝብ ልማት  ተብሎ ነው የመጣነው፣ እናንተማ ካልፈለጋችሁት እኛ እዚህ ምን እናደርጋለን?” በማለት ሰራተኞቹ  አካባቢውን ለቀው በመውጣታቸው፣ በአሁኑ ጊዜ ስራው ሙሉ በሙሉ ቆሟል።
መንግስት ስራው ተቋርጧል በማለት ለአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገርም፣ ህዝቡ ግን ሚጢቆ በሚባል ቦታ ላይ የተተከሉት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ጄኔሬተሮች ካልተነሱ ስራው መቋረጡን ከልብ አምነን ለመቀበል  አንችልም የሚል መልስ ሰጥቷል።
የአካባቢው ህዝብ አሁንም ጄኔሬተሮቹ እስኪነሱ ድረስ በትእግስት በአካባቢው ተገኝቶ እየጠበቀ ነው። ህዝቡ በስንቅ እጦት እንዳይቸገር እርስ በርሱ  እየተተካካ እንደሚጠብቅ ለማወቅ ተችሎአል።
የገዳሙ አባቶችከሀይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሀይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።በማለት ሰሞኑን ህዝቡን እየዞሩ ሲያስተምሩ ነበር። መንግስት የተወሰኑ መነኮሳትን አፍኖ መውሰዱም ታውቋል።
አሁን በሚታየው ስሜት የዋልድባ የስኳር ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል አንድ የአካባቢው ሰው ለኢሳት ተናግረዋል።” የህዝቡ ቁጣ ከመጠን እያለፈ ነውያሉት እኝህ ሰው መንግስት ከህዝቡ ጋር እልህ ውስጥ የሚጋባ ከሆነ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በግንባታው ዙሪያ የሀይማኖት አባቶች ስምምነታቸውን ሰጥተዋል ቢሉም፣ ህዝቡ ግን የሚቀበለው አልሆነም።የአቶ መለስ መንግስት ከህዝበ ክርስቲያኑ እና ሙስሊሙ ጋር በፈጠረው አለመግባባት በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን ምንጮች ከአዲስ አበባ ለ አዲስ ቪው ገልጸዋል።ይህንን ውጥረት ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተከታታይ ስብሰባ ላይ መሆናቸውም ተሰምቷል።

Saturday, April 28, 2012

በቴዲ አፍሮና በአዲካ መካከል አለመግባባት ተፈጠረ


ሪፖርተር 
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከአዲካ ኮሙዩኒኬሽንና ኢቨንትስ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡
ቴዎድሮስና አዲካ ውዝግብ ውስጥ የገቡት ‹‹ጥቁር ሰው›› በተሰኘው የቴዎድሮስ አዲሱ አልበም ከስፖንሰርና ከሽያጭ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ቴዲ አፍሮና አዲካ መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ.ም. ባደረጉት ውል፣ ቴዎድሮስ የአልበሙን ዋና ሲዲ (ማስተር ሲዲ) በአራት ሚሊዮን ብር ሸጧል፡፡ ክፍያውም በሁለት ጊዜ ተፈጽሟል፡፡ 

በዚህ ውል መሠረት አዲካ ያወጣውን ሙሉ ወጪ ከመለሰ በኋላ ከሚገኘው የተጣራ ትርፍ ቴዎድሮስ 20 በመቶ ገቢ ያገኛል፡፡ ይህም ለአምስት ዓመታት የሚቀጥል ሆኖ፣ ከአምስት ዓመት በኋላ በሲዲው ላይ ያለው ሙሉ መብት ከአዲካ ወደ ቴዎድሮስ ይዛወራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በውሉ መሠረት አዲካ ስፖንሰር የመፈለግና በህትመቱ ላይም የስፖንሰሩን ማስታወቂያ የመጠቀም መብት ይሰጠዋል፡፡ በቴዲና በአዲካ መካከል በዋናነት አለመግባባቶች የተፈጠሩት በእነዚህ ነጥቦች ዙርያ ሲሆን፣ አለመግባባታቸውም እየከረረ መምጣቱን ምንጮች እየገለጹ ነው፡፡ በአለመግባባቱ ውስጥም የሦስትዮሽ ውል የፈረመው ቤሌማ ኢንተርቴይመንት ኩባንያም ሌላኛው ተዋናይ ነው፡፡

ለቴዲ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች እንደሚገልጹት፣ ቴዲ በሲዲው ላይ የሜታ ቢራ ማስታወቂያ ይለጠፋል ብሎ አላሰበም፡፡ ነገር ግን ሲዲው በሚታተምበት ወቅት የሜታ ቢራ ማስታወቂያ በዋናው ሲዲ ላይ ተለጥፎ የተመለከተው ቴዲ ‹‹ሙዚቃዬን ትልልቅ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ሕፃናትም ያዳምጡታል፤ ለሕፃናቱ የመጠጥ አርዓያ መሆን አልፈልግም፤›› የሚል ሐሳብ በመሰንዘሩ፣ የሜታ ቢራ ማስታወቂያ የተለጠፈበት ኮፒ እንዲወገድ ብሎም ለገበያ እንዳይቀርብ ስምምነት ላይ ይደረሳል፡፡ በቴዲ በኩል ያሉ መረጃዎች የሜታ ቢራ ዓርማ የተለጠፈባቸው ሲዲዎች ብዛት 120 ሺሕ ነው ቢባልም፣ በአዲካ በኩል ግን 87 ሺሕ ኮፒዎች ናቸው፡፡

‹‹በውላችን መሠረት የስፖንሰሩ ጉዳይ ይመለከተናል፤ ለእኛ ግን ምንም የቀረበልን ሐሳብ የለም፤›› ሲሉ የቤሌማ ኢንተርቴይመንት ኩባንያ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወሰን አበጀ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሚያዝያ 6 ቀን 2004 ዓ.ም. ለሚሠራጨው ሲዲ ማስተር ሲዲውን አሥር ቀን እየቀረው የተረከበው አዲካ፣ ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶበታል በሚል ሲዲው ላይ ያለውን የሜታ ማስታወቂያ በማርከር በማጥፋት ለገበያ አቅርቧል፡፡ ይህ የተደረገው ብቸኛው ስፖንሰር የተባለው የሜታ ቢራ ፋብሪካ ይሁንታ በመገኘቱ ነው ሲሉ፣ የአዲካ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዋድ መሐመድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በገበያ ውስጥ ይህ የተደለዘ ሲዲ መሠራጨቱን የተመለከተው ቴዲ በሁኔታው ደስተኛ አለመሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሌላኛው አለመግባባት ቴዎድሮስ የታተመውን የሲዲ ቁጥር ማወቅ አለመቻሉ ነው ተብሏል፡፡ የቴዎድሮስን ሐሳብ አቶ ወሰንም ይጋራሉ፡፡ 

ቴዲና አዲካ ባላቸው ስምምነት መሠረት ‹‹ጥቁር ሰው›› አልበም ከሚያስገኘው የተጣራ ትርፍ ገቢ ውስጥ 20 በመቶ ለቴዲ አፍሮ የሚከፈል ነው፡፡ የተጣራ ትርፍ መኖሩን ለማወቅ ከሚያገለግሉ ነገሮች አንዱ የታተመውን የሲዲ ቁጥር ማወቅ ነው፡፡ በመጀመርያዎቹ የህትመት ወቅቶች የተዘረጋው የሞባይል አጭር መልዕክት (SMS) ሲላክ የሚጻፍ ሲሪያል ቁጥር ታትሞበታል፡፡ ቴዎድሮስ የሲርያል ቁጥሩ ቢቀጥል የታተመውን የሲዲ ብዛት ማወቅ ያስችላል ብሎ ያምናል፡፡

በሚቀጥሉት የሲዲ ህትመቶች ግን ምንም ዓይነት ሲሪያል ቁጥር ታትሞ ለገበያ እንዳልቀረበ የሪፖርተር መረጃዎች ይገልጻሉ፡፡ በተዘዋዋሪ መንገድ ከቴዎድሮስ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ቴዎድሮስ ሙሉ ትኩረቱን ሙዚቃው ላይ ከማድረጉ ባሻገር የቢዝነስ ሥራዎችን ማኔጀሩ አቶ አዲስ ገሠሠ ያካሂዳሉ፡፡ ያም ሆኖ ግን ቴዎድሮስ በሁኔታው ደስተኛ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

ቴዎድሮስ ዝርዝር መረጃዎችን ከማኔጀሩ ማግኘት እንደሚቻል ቢገልጽም፣ የሪፖርተር መረጃዎች እንደሚሉት ቴዎድሮስና ማኔጀሩ መግባባት ተስኗቸዋል፡፡ ከማኔጀሩ ከአቶ አዲስ ገሠሠ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ከቴዎድሮስ ጋር መግባባት ያልተቻለው ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በቴዲ የመቃወሚያ ነጥቦች አዲካ ኮሙዩኒኬሽን በፍፁም እንደማይስማማና ይልቁንም የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ብዙ ርቀት መሄዱን፣ የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዋድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በመጀመርያ አዲካ የሜታ ቢራን ማስታወቂያ በሲዲው ላይ ለማተም የውል ስምምነቱ ይፈቅድለታል፡፡ ‹‹ነገር ግን ቴዎድሮስ ሕፃናት ሙዚቃዬን ይሰማሉ ማለቱን እንደ መልካም ነገር ወስደን ከሲዲው ላይ አጥፍተነዋል፡፡ ካለን ጊዜ አንፃር ሲዲው ጥቅም ላይ እንዳይውል ቢባልም በደረስንበት ወቅታዊ ስምምነት ማስታወቂያውን አጥፍተን ገበያ ላይ አውለነዋል፤›› ሲሉ አቶ አዋድ ገልጸዋል፡፡

‹‹ሲዲው ለገበያ የሚቀርብበት በጣት የሚቆጠሩ ጊዜያት ብቻ ነበሩን፤ ጊዜ ወሳኝ ነበር፤›› ሲሉ አቶ አዋድ የወቅቱን አንገብጋቢነት አስረድተዋል፡፡ ማሽኑ በቀን የማተም አቅሙ ከ20 ሺሕ እስከ 25 ሺሕ ሲዲ ነው፡፡ በዚህ የማምረት አቅም የሜታ ማስታወቂያ የተለጠፈበትን 87 ሺሕ ኮፒ ማስወገድ የሚቻል ነገር አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

ሲሪያል ቁጥር የተሰጠው ለግጥሞቹ ነው ተብሎ አዲካ፣ የኦዲዮ ቪዥዋል አሳታሚዎች ማኅበርና የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በመተባበር ማንኛውም ሰው ኦሪጂናል መግዛቱ የሚታወቅበትና በዚህም የሚሸለምበት አሠራር ነው የተዘረጋው ያሉት አቶ አዋድ፣ ‹‹በነበሩን ጥሩ የሥራ ግንኙነቶች ምክንያት ብሔራዊ ሎተሪ ፈቃድ እንደሚሰጥ ታሳቢ ተደርጎ ህትመት ቢጀመርም፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ ብሔራዊ ሎተሪ ፈቃድ ከልክሏል፤›› ሲሉ የሲሪያል ቁጥር በመጀመርያዎቹ ህትመቶች መካተቱንና በተከታዮቹ ህትመቶች ላይ መቋረጡን ያስረዳሉ፡፡

‹‹የሲሪያል ቁጥር የታተመው የሲዲ ኮፒ ብዛቱን ለማወቅ አይደለም፤›› ሲሉ አቶ አዋድ ይገልጻሉ፡፡ አንድ ባዶ ሲዲ የሚገዛው በአራት ብር ነው፡፡ የሲዲ መሸፈኛ (ከቨር) አምስት ብር ነው፡፡ የግጥሙ ህትመት ዋጋውም የዚያኑ ያህል ነው፡፡ ከአንድ ሲዲ የሚገኘው ትርፍ ስድስት ብር ነው፡፡ በእስካሁኑ ሒደት የታተመው ሲዲ የወጣበት ወጪ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን፣ አዲካ ሙሉ ወጪውን ከሸፈነ በኋላ ከሚያገኘው የተጣራ ትርፍ ውስጥ 20 በመቶው ለቴዎድሮስ ገቢ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን የካሴት ህትመቱ የትና እንዴት እንደተካሄደ ለቴዲ እንቆቅልሽ ሆኖበታል፡፡ ለገበያ ቀረበ የተባለውን የሲዲ ቁጥር እንደማያምንበት ቴዎድሮስ ተናግሯል፡፡ ቴዎድሮስ ከውጭ አገር የታተመ ሲዲ ገብቷል ብሎ ከማመኑም በተጨማሪ፣ ለውጭው ዓለም በምን መንገድ ሲዲው እንደተሠራጨ አሁንም ቴዲ ይጠይቃል፡፡

አቶ አዋድ ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች በተመሰከረለት ባለሙያ ኦዲት ይደረግ መባሉን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ሒደትም ላይ ኤችኤስቲ የተሰኘው ኩባንያ ተመርጦ ወደ ኦዲቲንግ ሥራ በመግባት ላይ እያለ ቴዎድሮስ ኦዲቲንጉ እንዲቆም ማድረጉ ተሰምቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሁለቱ ወገኖች አለመግባባት በጡዘት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የተለያዩ አካላት በሽምግልና ለመገላገል እየሞከሩ መሆኑ ታውቋል፡፡