አዲስ ቪው ሚዲያ
ኤፕሪል 27 2012
የ2012 PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award አሸናፊ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሽልማት ላይ ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም
ፋሲል እንደምትገኝ የአዲስ ቪው ምንጮች ገለጹ።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
በሽብርተኝነት ተከሶ ጉዳዩን በፍርድ ቤት እየተከታተለ ባለበት ወቅት “ፔን ፍሪደም አዋርድ” የተባለውን አለም አቀፍ ሽልማትን አግኝቷ።ፔን
አሜሪካን ሴንተር የተባለው አለማቀፍ ድርጅት ጋዜጠኛ እስክንድር ለሰራቸው ስራዎች እውቅና በመስጠት ለ26ኛውን ሽልማት
ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።
ፔን አሜሪካን ሴንተር
ባዘጋጀው እና ሜይ 1 2012 በኒውዮርክ ሲቲ American
Museum of Natural History በሚካሄደው
የሽልማት ፕሮግራም ላይ የጋዜጠኛ እስክንድር ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካልም ተጋባዥ ሆና እንደምትገኝ እና ሽልማቱንም ትቀበላለች ተብሎ
ይጠበቃል።
ከሰርካለም በተጨማሪ
የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ የሆኑ ድርጅት ሀላፊዎች እንዲሁም የቀድሞ አንድነት ሊቀመንበር የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የዝግጅቱ
ታዳሚዎች እንደሚሆኑ ታውቋል። ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በ2007 Courage
in Journalism Award የተሰኘውን ሸልማት ከ IWMF (International
Women's Media Foundation) ማግኘቷ እና ከሽልማቱ ያገኘችውን ገንዘብ
ለአምንስቲ ኢንተርናሽናል መለገሷ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment